በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ወደ ሀገር ለመመለስ እየተሰራ ቢገኝም አስቸጋሪ ሁኔታ እንዳለ እያወቁ የስራ እድል አለ በሚል የሚሄዱ ዜጎች እያጋጠሙት መሆኑን ዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ
ሆኖም በህጋዊ መንገድም ሄደዉ ችግር የሚያጋጥማቸው ኢትዩጵያውያን መብት ለማስጠበቅ ቆንስላ እና ኢምባሲ ትኩረት ሰጥተዉ እንዲከታተሉ ቋሚ የስራ መመሪያ ተሰጥቷል ተብሏል።
ኢትዮጲያዉያኑ ክብር እና መብት ተጠብቆ እንዲቆዩ ከሚሲዩን መሪዎች በተጨማሪ ይህንን ጉዳይ ብቻ እንዲከታተሉ ዲኘሎማቶች መመደባቸዉን የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዩን ጢሞቴዎስ ተናግረዋል።
ከማይናማር በተጨማሪ በሳዉዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታዉ ነበሩ የተባሉ 26 ሺህ ዜጎችን በአምስት ወራት ዉስጥ ማስመለሱን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ለስራ የተጓዙ ኢትዮጵያዉያን ከአንድ የስራ ቦታ ወደ ሌላ የስራ ቦታ ለመለወጥ ወይም ወደ ሀገር ለመመለስ እንዲሁም የካሳ ክፍያ እንዲያገኙ እንዲሁም ከደሞዝ ጋር የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነዉ ተብሏል።
በጅዳ ÷ ራያድ ÷ አቡዳቢ ÷ ዱባይ እንዲሁም በኩዌት ቆንስላ ፅ/ቤት ይህንን ለማድረግ እየተሰራ ነዉ ብለዋል።
ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ያልሄዱ እና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ የስራ ስምምነት ያላደረገችበት የስራ ጉዞ ያደረጉ ዜጎች ለዘርፈ ብዙ ጥቃት የዳረጉ መሆናቸዉ ተገልፆል።
የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ጌዲዩን ጢሞቴዎስ ዛሬ በእንደራሴዎቹ ምክር ቤት ተገኝተው ከአባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ቁምነገር አየለ
ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም
