ከ1መቶ 40 በላይ ሲቪል ማህበራት በመጪዉ ምርጫ ሚናቸዉን ለመዉጣት ተመዝግበው እየሰሩ እንደሚገኝ ተገለፀ

ምርጫ ህጋዊ እና ግልፅ እንዲሆን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ያላቸዉን ሚና እንዲወጡ ያስፈልጋል ተብሏል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ኘሬዝደንት አቶ አህመድ ሁሴን፤ በምርጫዉ ሂደት በነፃነት ተንቀሳቅሶ ለመስራት ምርጫ ቦርድ ድርጅቶቹን መመዝገብ እንደሚያስፈልገዉ ገልፀዋል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ የነበራቸዉ ኘሬዝዳንቱ ስለ ምርጫዉ ማኅበረሰቡ መረጃ እንዲኖረው እና ግንዛቤ እንዲያገኝ እንዲሁም በሂደቱ ውስጥ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና እንዳለቸዉ ገልፀዉ ምቹ ምህዳር እንዲፈጠርላቸዉ ጠይቀዋል።

በምርጫ ሂደት የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ተሳትፎን እና የዝግጅት ዉጤታማነት የሚገቱ መሠናክሎች እንዲለዩ መጠየቁ ይታወሳል።

ቁምነገር አየለ

ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *