በደቡብ አፍሪካ ለክረምት ወራት በሚከናወን ባህላዊ የግርዛት ሥነ-ሥርዓት ላይ ተሳትፈው የነበሩ 41 ወጣቶች ሕይወታቸው አለፈ

የአገሪቱ መንግሥት እንዳስታወቀው፣ አብዛኞቹ ሞቶች የተመዘገቡት በምሥራቃዊ ኬፕ ግዛት ነው።

ለወጣቶቹ ህልፈት እንደ ዋና ምክንያት የተጠቀሱት በግርዛቱ ወቅት የሚያጋጥም ከፍተኛ የደም መፍሰስ እና የቁስል ኢንፌክሽን መሆናቸው ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም፣ በሥነ-ሥርዓቱ ወቅት የሚጣሉ ጠንካራ የውሃ እቀባዎች ለድርቀት እንዲሁም የመቆያ ስፍራዎቹ ለከፍተኛ ብርድ የተጋለጡ መሆን ለህልፈቱ ተጨማሪ ምክንያቶች መሆናቸው ተነግሯል።

የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ይህን ጥንታዊ የሽግግር ባህል ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ ጥረት ቢጀምርም፣ ሕገ-ወጥ የግርዛት ጣቢያዎች መስፋፋት ለችግሩ መባባስ ምክንያት ሆኗል ተብሏል።

የአገሪቱ የባህላዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር በበኩሉ፣ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገልጾ፣ ፈቃድ ሳይኖራቸው ሥነ-ሥርዓቱን በሚያከናውኑ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

ይህ የግርዛት ክንውን በደቡብ አፍሪካ የኮሳ ብሔረሰብ ዘንድ፣ ወንዶች ልጆች ወደ ጎልማሳነት የሚሸጋገሩበት ትልቅ ባህላዊ ሥነ-ሥርዓት ተደርጎ ይወሰዳል።

ልዑል ወልዴ

ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *