ቼልሲ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካን ከሀላፊነታቸው ማንሳቱን ታወቀ።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት የክለቡ ከፍተኛ የቦርድ አመራር አባላት ዛሬ ከሰዓታት በኋላ ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ ነው።

በዚህም መሰረት የፊታችን እሁድ ወደ ኢትሃድ አምርተው ማን.ሲቲን በሚገጥሙበት ጨዋታ ቡድኑን እንደማይመሩት ተረጋግጧል።

ክለቡ የእሳቸውን ምትክ በማፈላለግ ላይ መሆኑም ተሰምቷል። ጣልያናዊው በበኩላቸው በመጪው ክረምት የፔፕ ጋርዲዮላ ተተኪ በመሆን ወደ ኢትሃድ እንደሚያመሩ ተገምቷል።

ማሬስካ ካለፉት ሰባት የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት አንድ ጨዋታ ብቻ ነው። በዚህም ከደጋፊዎቻቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ሲገጥማቸው ቆይቷል።

ምስጋናው ታደሰ

ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *