የማሪን ሌ ፐን የፖለቲካ እጣ ፈንታ በፈረንሳይ ፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

የፈረንሳይ ቀኝ ዘመም ፖለቲከኛ ማሪን ሌ ፐን፣ ለ5 ዓመታት ከምርጫ እንዲታገዱ የተላለፈባቸውን ውሳኔ ለመቃወም ያቀረቡት የይግባኝ ክርክር በፓሪስ መታየት ተጀምሯል።

ሌ ፐን ባሳለፍነው አመት የ2.9 ሚሊዮን ዩሮ የአውሮፓ ህብረት ገንዘብን ለፓርቲያቸው ጥቅም አውለዋል በሚል ባለፈው ዓመት ጥፋተኛ መባላቸው ይታወሳል።

በወቅቱ ከተላለፈባቸው የ4 ዓመት እስራት ውስጥ ሁለቱ አመት በገደብ እና የ100,000 ዩሮ መቀጮ የተወሰነባቸው ሲሆን፣ ከማንኛውም የፖለቲካ ምርጫ እንቅስቃሴም እንዲታገዱም ፍርድ ተላልፎባቸዋል።

ይህ እገዳ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ካልተነሳ፣ ሌ ፐን በ2027 በሚካሄደው የፈረንሳይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መወዳደር የማይችሉ ሲሆን።

የ”ናሽናል ራሊ” ፓርቲ መሪ ጆርዳን ባርዴላ ውሳኔውን “ዲሞክራሲን የሚጎዳ” ሲሉ ገልፀው ሌ ፐን ንጽህናቸውንን እንደሚያረጋግጡም ተናግረዋል።

በፓሪስ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሚካሄደው ይህ ክርክር እስከ የካቲት 12 የሚቆይ ሲሆን፣ የመጨረሻው ውሳኔ ግን ከክረምት በፊት አይጠበቅም። ይህም ከሚቀጥለው ዓመት ምርጫ ቀደም ብሎ ውሳኔ እንደሚሰጥ ያሳያል ሲል የዘገበው BBC ነው።

ሀና ሰይፉ

ጥር 05/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *