የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከገቢ ምርት ጥገኝነት ወደ አምራችነት ሊሸጋገር ይገባል ተባለ፡፡

ኢትዮጵያ ከውጭ አስመጪነት ወደ አምራችነት  በመሸጋገር የውጭ ምንዛሬ ጫናን መቀነስ እንዳለባት  የፋይናንስ አማካሪ የሆኑት አቶ ጥላሁን ግርማ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና የንግድ ሚዛን መዛባት መፍትሄ እንዲያገኝ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ እንደሚያስፈልግም ባለሙያው ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከጫማና ልብስ እስከ ማዳበሪያ ያሉ መሰረታዊ ፍላጎቶቿን ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ጥገኛ ማድረጓ ለችግሩ ዋነኛ መንስኤ ናቸው ብለዋል፡፡

እንደ ጨርቃጨርቅ ላሉና ቀላል ቴክኖሎጂ ለሚጠይቁ ዘርፎች ትኩረት ሰጥቶ ወደ አምራችነት በመሸጋገር የውጭ ምንዛሬ ጫናን መቀነስ ላይ መስራት እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል።

ለማዳበሪያ ግዢ የሚወጣውን ዶላር ለማዳን በሶማሌ ክልል የሚገነባው የማዳበሪያ ፋብሪካን የመሰሉ ሀገር በቀል ጥረቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም አቶ ጥላሁን አንስተዋል፡፡

የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ምርትን በሀገር ውስጥ መተካት ብቸኛው አማራጭ መሆኑንም ባለሙያው ጠቁመዋል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ጥር 07/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *