በተለያየ የህገ-ወጥ መንገድ በተሰማሩ ዜጎች እና በተለይ ሰነድ ሲያጭበረብሩ የተገኙ 6,395 የዉጭ ዜጎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል፡፡
በተለያየ የህገ-ወጥ መንገድ የተሰማሩ 99 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተነገረም ሲሆን ሲሆን 83 የዉጭ ሀገራት ዜጎችን ተጠያቂ በማድረግ 11 ቤቶች መታሸጋቸው ተነግሯል፡፡
ሰነድ በማጭበርበር 6,395 የዉጭ ዜጎች እና 3,126 በሚሆኑ ኢትዮጵያውያ ላይ እርምጃ መወሰዱን የገለፁት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ናቸው፡፡
ዳይሬክተሯ በስድስት ወራት ወስጥ ከ 3 ሚለዮን በላይ ለሚሆኑ ተጓዦች አገልግሎት ተሰጥቷል ብለዋል ።
ከ800ሺህ በላይ ደንበኞችም በቅርንጫፍ ብቻ ለአዲሱ ኢ-ፓስፖርት ማመልከታቸውን አስታውቀዋል፡፡
የኢ-ፓስፖርት አገልግሎት በሁሉም ቅርንጫፎች መሰጠት በመጀመሩም ከ800ሺህ በላይ ደንበኞች በቅርንጫፍ ብቻ ለአዲሱ ኢ-ፓስፖርት ማመልከታቸው በተቋሙ የስድስት ወራት ሪፖርት ግምገማ ላይ ተገልጿል።
ጥር 07/2018 ዓ.ም
