አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ በቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነት፣ በተዋናይነትና በሌሎች የጥበብ ስራዎቹ በኪነ ጥበቡ ቤተሰብ ዘንድ ይታወቃል።
ሁለገቡ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ለበርካታ ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሚተላለፈውን የቤተሰብ ጨዋታ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ በመሆን እያገለገለ ነበር።
አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ በፊልም እና በቴአትር ስራዎቹ እጅግ ተወዳጅ የነበረ ሲሆን፤ ሲቲ ቦይዝ፣ ሳልነግራት፣ ያንቺው ሌባ 2፣ ኤፍቢአይ፣ ሚስተር ኤክስ፣ ቾምቤ እና ሌሎችም ድንቅ ብቃቱን ያሳየባቸው ፊልሞች ናቸው።
ፍሬሽ ማን ከህዝብ ጋር ያስተዋወቀው የቴአትር ስራው ነው።
አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት ነበር።
ኢትዮ ኤፍኤም በተወዳጁ አርቲስት ድንገተኛ ሞት የተሰማውን ሀዘን ይገልጻል ።ለወዳጅ ዘመዱቹ እና አድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል ።
ጥር 8/2018 ዓ.ም
