በአሜሪካ በደረሰው ከባድ የበረዶ ማዕበል ከ8መቶ ሺህ በላይ ሰዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋረጠባቸዉ

ሰኞ ዕለት አገሪቱን በመታው ከባድ የበረዶ ማዕበል ምክንያት በመላው አሜሪካ ከ8መቶ21 ሺህ በላይ ሰዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦባቸዋል።

ከፍተኛው የኃይል መቋረጥ የተመዘገበው በቴነሲ ግዛት ሲሆን፤ እዚያም እስከ 2መቶ55 ሺህ 4መቶ52 የሚደርሱ ደንበኞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦባቸዋል ነዉ የተባለዉ።

የብሔራዊ የአየር ሁኔታ አገልግሎትን ዋቢ በማድረግ ጂቢ ኒውስ እንደዘገበው፤ 17 ግዛቶች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጁ ሲሆን፤ የአደጋ ጊዜ ቡድኖችን እና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ዝግጁ ማድረጋቸዉ ተገልጿል፡፡

ከፍተኛ የበረዶ ዝናብ ባልደረሰባቸው አካባቢዎች ሳይቀር አደገኛ የበረዶ ክምችት ሊከሰት እንደሚችል የአየር ሁኔታ ትንበያ ባለሙያዎች ማስጠንቀቃቸውን የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

በዚህ ከባድ የበረዶ ማዕበል ምክንያት ትናንት የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተዘግቧል።

በመላው አሜሪካ ከ16 ሺህ በላይ በረራዎች የተሰረዙ ሲሆን፤በአገሪቱ በሚገኙ አየር ማረፊያዎች ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ በረራዎች ተጓትተዋል ያለዉ ቢቢሲ ነዉ።

እስከዳር ግርማ

ጥር 18/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *