የሕክምና ትምህርት ቤት ለመግባት ሲል የገዛ እግሩን የቆረጠው ወጣት

አስደናቂ እና ያልተለመዱ ክስተቶችን መስማት አዲስ ካልሆነባት ህንድ አለምን ድንጋጤ እና ግርምት ውስጥ የከተተ ዜና ተሰምቱዋ ነገሩ የተከሰተው በህንዱዋ ግዛት ኒው ዴልሂ ነው፡፡

የሕክምና ትምህርት ቤት ለመግባት ያለው ከፍተኛ ጉጉት ወደ አስከፊ ውሳኔ የመራው የ20 ዓመቱ ሱራጅ ባስካር፣ በራሱ ላይ በፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት መላውን የህንድ ማህበረሰብ አስገርሟል።

ከኡታር ፕራዴሽ ግዛት የመጣው ይህ ወጣት፣ የህንድ የሕክምና መግቢያ ፈተናን (NEET) ለሁለት ጊዜያት ቢፈተንም ለማልፍ ገን ይቸገራል ፤ይሁን እንጂ ተስፋ ባለመቁረጥ፣ ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጠውን የ5 በመቶ የኮታ ዕድል ተጠቅሞ ለመግባት ያስባል አስቦም አልቀረ ወደተግባር ያመራል በመሆኑም የገዛ እግሩን ቆርጦ በመጣል እራሱ ላይ የአካል ጉዳት ያደርሳል

ወጣቱ ድርጊቱን በራሱ ላይ የፈጸመው ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ጥቃት እንደደረሰበት በማስመስል ነበር፤ በወቅቱ ታላቅ ወንድሙ አክሽ ባስካር ለፖሊስ በሰጠው ቃል፣ ወንድሙ ካሊልፑር በተባለ መንደር ውስጥ ጥቃት ደርሶበት እግሩተቆርጦና ራሱን ስቶ መገኘቱን ተናግሮ ነበር።

ጉዳዩ ሪፖርት የተደረገለትፖሊስ ባደረገው ጥልቅ ምርመራ ግን በወጣቱ ታሪክ ውስጥ በርካታ የማይገጣጠሙ ነጥቦችን ያገኛል፤የአካባቢው ፖሊስ ቃል አቀባይ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፦”ተከሳሹ የተቀነባበረ ታሪክ በመንገር ምርመራውን ለማሳሳት ሞክሮ ነበር፤ ነገር ግን የቀረቡት ማስረጃዎችና የተደረገው ጥያቄ ድርጊቱን እራሱ እንደፈጸመው አረጋግጠዋል።” ብለዋል

ፖሊስ በምርመራ በሚያደርግበት ወቅት ጠከሳሽ የማስታወሻ ደብተሩ ላይ “በ2026 የሕክምና ዶክተር እሆናለሁ” ብሎ እንደፃፈ ተመልክተዋል።

በተጨማሪም የእግሩ አቆራረጥ በማሽን የተከናወነና እጅግ የጠራ በመሆኑ፣ በድንገተኛ ጥቃት ሊከሰት እንደማይችል መሆኑን ሃኪሞች አረጋግጠዋል።

ድርጊቱ ከተፈጸመበት ቦታ በቅርብ አርቀት ላይ እራሱን ለማደንዘዣ የተጠቀመባቸው መርፌዎችንም አግኝተዋል።

ወጣቱ በአሁኑ ወቅት በህክምና ማዕከል ውስጥ ክትትል እየተደረገለት ሲሆን፣ የተቆረጠው እግሩ እስካሁን አልተገኘም።
ፖሊስ በወጣቱ ላይ ምን ዓይነት ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ግራ ተጋብቷል፤ ምክንያቱም ድርጊቱ እጅግ አሰቃቂና ያልተለመደ በመሆኑ ነው።

ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ፣ ወጣቱ በፈተና ማለፍ አቅቶት የሕክምና ትምህርት ቤት ለመግባት የከፈለዉ ይህ ዋጋ፣ በቀሪው ዘመኑ በአንድ እግር እንዲኖር የሚያስገድደው በመሆኑ በራሱ ትልቅ ቅጣት መሆኑን የኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ጥር 20/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *