ግዙፉ የመደሀኒት አምራች ኩባንያ አስትራዜኒካ የኮቪድ-19 ክትባት ለሙከራ እስከ 400 ሚሊዮን ዶዝ ለማቅረብ ከአውሮፓውያን ጋር አካባቢያዊ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
ተነሳሽነቱ ከአውሮፓ ሀገራት ጋር የተገባ ሁሉን አቀፍ ስምምነት መሆኑን የገለፀ ሲሆን ክትባቱን ለሚፈልጉ የአውሮፓ አገራት ሁሉ እንዲያገኙና ሁሉንም አካታች ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡
የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ተደራሽነት ለማፋጠን ጀርመን ፤ ፈረንሳይ ፤ ጠሊያንና ኔዘርላንድ እንደ አውሮፓውያኑ 2020 መጨረሻ ድረስ ያገኛሉ ተብሏል፡፡
የሲውዲን ኩባንያ የሆነው አስትራዜኒካ በቅርቡ ከእንግሊዝ ጋር ተመሳሳይ ስምምነት ፈርሟል፡፡
ከአሜሪካ ጋርም የ700 ሚሊዮን የክትባት ህብረት ስምምነት መያዙ ይታወቃል፡፡
እንዲሁም ከሴሩም ኢንስቲትዩት ኦፍ ኢንዲያን ጋር ተጨማሪ 1 ቢሊዮን ዶዝ ለማቅረብ መስማማቱ አይዘነጋም፡፡
ሞዴርናና ሳኖፊን ጨምሮ ሌሎች ኩባንያዎች በአዲሱ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከላከል ዙሪያ ክትባቶችን ለማምረት እየጣሩ ነው፡፡
ባለሞያዎች እንደሚሉት እነዚህ ጥረቶች በሕዝብ ሕይወት ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለማስቀረትና ተጨማሪ በቫይረሱ የሚጠቁ ዜጎችን ቁጥር ለማስቀረት አስፈላጊ መሆኑን አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በደረሰ አማረ
ሰኔ 8 ቀን 2012 ዓ.ም
