ብረት 36 በመቶ፣ ሲሚንቶ 28 በመቶ ዕድገት አሳይተዋል የተባለ ሲሆን፤ ለዚህም እንደምክንያት የተነሳዉ በተለያዩ ጊዜ ዘመናዊ ቤቶች እየተገነቡ መሆኑ ነዉ፡፡
ይህ የተባለዉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ባለበት ነዉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስትን የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እያቀረቡ ሲሆን፤ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ ይገኛል፡፡
በአገልግሎት በኩልም መሻሻሎች መኖራቸዉን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በምሳሌነት ያነሱት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ነዉ፡፡
ከለዉጡ በፊት በአመት 8 ሚሊየን ሰዉ ያጓጉዝ እንደነበር አንስተዉ፤ ባለፉት ስድስት ወራት 10.7 ሚሊየን ሰዎችን መጓጓዝ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በዚህ አመት በትንሹ 22 ሚሊየን ሰዎችን ማጓጓዝ የምንችልበት ደረጃ እንደርሳለን ብለዋል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
ጥር 26/2018 ዓ.ም
