ይህ ህዝብ መድረክ እንጅ ተዋናይ መሆን አልቻለም ብለዋል።
የትግራይ ህዝብ ከመድረክነት ወጥቶ ተዋናይ ለመሆን ራሱን እንደ አዲስ መቃኘት እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
መቀሌ እንደሌሎች ከተሞች በዚህ ሶሰት አመት ተሰርታ ብትሆን አሁን ያለችበት ሁኔታ ጥሩ ይሆን እንደነበረ አንስተዋል፡፡
ህዝቡ ወደ ቤቱ ይግባ፣ ስራዉን ይስራ እኛ የፓለቲካ ፓርቲዎች እንጨቃጨቅ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ ህዝብ እየተሰቃየ አይሆንም ብለዋል፡፡
በትግራይ ክልል ያሉ የፓለቲካ ፓርቲዎች ያሉበትን ደረጃ ማሻሻል አለመቻላቸዉንም እንደ ችግር አንስተዋል፡፡
የትግራይ ህዝብ በዚህ ሰዓት ሰላምና ልማት እንደሚያስፈልገዉና ጦርነት እንደሚበቃዉ ተናግረዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት አካሂዷል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
ጥር 26/2018 ዓ.ም
