ፈነርባቼ የቀድሞውን የቼልሲ አማካይ ንጎሎ ካንቴን ከሳውዲው አል-ኢቲሀድ ክለብ ማስፈረሙን በይፋ አረጋግጧል።

ይህ ዝውውር ማክሰኞ ዕለት የተሰረዘ መስሎ ነበር፤ በወቅቱ ፈነርባቼ ባወጣው መግለጫ ለዝውውሩ መስተጓጎል አል-ኢቲሀድን ተጠያቂ አድርጎ ነበር።

እንደ ክለቡ ገለፃ አል-ኢቲሀድ የሞሮኮውን አጥቂ ዩሱፍ ኤን-ነሲሪን በልውውጥ ወደ ሳውዲ እንዲሄድ የሚያደርገውን አስፈላጊ የዝውውር ሰነድ በወቅቱ አላጠናቀቀም በሚል በሳውዲው ክለብ ላይ ወቀሳውን ሰንዝሮነበር።

ይሁን እንጂ ዛሬ (ረቡዕ) ክለቡ ባወጣው መግለጫ ችግሩ መፈታቱንና የቀድሞው የቼልሲ ኮከብ ካንቴ በሳውዲ አረቢያ ለሁለት ዓመት ተኩል ከቆየ በኋላ ወደ ቱርክ በማቅናት ፌኔርባቼን መቀላቀሉን አስታውቋል።

የ34 ዓመቱ ፈረንሳዊው ንጎሎ ካንቴ በቼልሲ በነበረው ቆይታ የሻምፒዮንስ ሊግ፣ ፕሪሚየር ሊግ፣ ዩሮፓ ሊግ እና ኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል። ከዚያ በፊት ደግሞ ሌይስተር ሲቲ ታሪካዊውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ እንዲያነሳ ትልቅ አስተዋጽኦ ነበረው።

ምስጋናው ታደሰ

ጥር 27/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *