አሜሪካ በምስራቅ ፓሲፊክ በሌላ ጀልባ ላይ ጥቃት ሰንዝራ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

እንደ አሜሪካ ደቡባዊ ዕዝ መግለጫ ከሆነ፤ የአሜሪካ ጦር ሐሙስ ዕለት በምስራቅ ፓሲፊክ ውቅያኖስ ውስጥ ዕፅ ያዘዋውራል ተብሎ በተጠረጠረ ሌላ ጀልባ ላይ በፈጸመው ጥቃት የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።

ደቡባዊ ዕዝ በኤክስ ገጹ ላይ ባሰፈረው መረጃ የደቡባዊ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኤል ዶኖቫን በሰጡት መመሪያ መሰረት፤ ‹‹ጆይንት ታስክ ፎርስ ሳውዘርን ስፒር ›› ሽብርተኛ ተብለው በተፈረጁ ድርጅቶች በሚንቀሳቀስ ጀልባ ላይ ጥቃት ፈጽሟል ብሏል።

በጥቃቱ ወቅት በአሜሪካ ወታደራዊ አባላት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም አክሎ ገልጿል።

ጄኔራል ዶኖቫን የደቡባዊ ዕዝ አመራርን የተረከቡት በዚሁ ሐሙስ ዕለት ነበር።

የትራምፕ አስተዳደር የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን ለመግታት ያለመ ነው ባለው እና ‹‹ኦፕሬሽን ሳውዘርን ስፒር›› ተብሎ በተሰየመው ዘመቻ፤ ዕፅ ያዘዋውራሉ ተብለው በሚጠረጠሩ ጀልባዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች እስካሁን ቢያንስ 1መቶ19 ሰዎች ተገድለዋል ሲል ኤን ኤን ዘግቧል፡፡

ሐመረ ፍሬዉ

ጥር 29/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *