ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሙስጠፋ፥በጋዛ ሰርጥ ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች በዌስት ባንክ ሊደገሙ እንደሚችሉ ተናግረዋል
የእስራኤልን መስፋፋት ለማስቆም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከባድ እና ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስድም ጥሪ አቅርበዋል።
ይህን ያሉት ከካናዳ፣እንግሊዝ፣የአውሮፓ ህብረት፣ኖርዌይ እና ኔዘርላንድ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት ነው።
ሙስጠፋ ሁለተኛውን የጋዛ የሰላም ሂደት ለማረጋገጥ የበለጠ ጦርነትን ለመከላከል፣መልሶ ለማገገም እና መልሶ ግንባታን ለማፋጠን ዓለም አቀፍ ጥረቶችን ጠይቀዋል ሲል አልጀዚራ ነዉ የዘገበዉ።
ሊዲያ ደሳለኝ
የካቲት 03/2018 ዓ.ም
