የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት 4.4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገለጸ

ገቢው ከዕቅዱ የሁለት በመቶ፤ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ደግሞ የ14 በመቶ ብልጫ እንዳለው ዋና ሥራ አስፈጻሚው መስፍን ጣሰው ገልጸዋል።

አየር መንገዱ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹን ከ145 በላይ እንዲሁም የሀገር ውስጦቹን 23 እንዳደረሰም ተናግረዋል።

በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ሰባት የተለያዩ አውሮፕላኖች ወደ ሥራ ገብተዋል፦ አንድ ኤ350-1000 ኤርባስ፣
ሁለት ኤ350-900፣ አንድ ቦይንግ 787-800፣ ሦስት ቦይንግ 737 ማክስ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚጠቀምባቸው አውሮፕላኖች 147 ደርሰዋል።

አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት ከ4 የአፍሪካ አየር መንገዶች ጋር በአጋርነት እየሠራ እንደሚገኝ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጨምረው ገልጸዋል።

የካቲት 03/20018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *