የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለ39ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው

39ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ  በመላው አፍሪካ የሚገኙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች  ወደ አዲስ አበባ መግባታቸውን  ቀጥለዋል።

ዛሬ የካቲት 4/2018 ጠዋት በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ  የደቡብ ሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞንዴ ሴማያ ኩምባ፤የጋናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሙኤል ኦኩዴዝቶ አብላክዋ፤
የሲሼልሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባሪ ፋውሬ፤የሴኔጋሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ ኒያንግ፤የቶጎው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮበርት ዱሴይ፤
የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲልቪ ቫለሪ ኖቴፌ ቦርን ባይፖ-ቴሞን፤የታንዛኒያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ ታቢት ኮምቦ ፤
የላይቤሪያዋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳራ ቤይሶሎ ኒያንቲ እንዲሁም የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኖኤላ ናክዊፖኔ አዬጋናጋቶ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ዛሬ ወደ መዲናዋ የገቡት ሚኒስትሮች  የጉባኤው አካል ሆኖ በዛሬው እለት  በሚጀምረው 48ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ይሳተፋሉ፡፡

ሚኒስትሮቹ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ የሁሉንም የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን የሚያገናኝ ሲሆን፣ በቁልፍ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ በመምከር ለመሪዎች ጉባኤ አጀንዳዎችን ያዘጋጃል።

ሀና ሰይፉ

የካቲት 04/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *