ትናንት ምሽት በሰርቢያ ቤልግሬድ በተካሄደው 6ኛ ዙር የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች ተወዳድረው ነበር፡፡

በ800 ሜትር ሴቶች አጭር ትራክ በምድብ 1 የተወዳደረችው ሃብታም ገበየሁ በስፔናዊቷ ሎሪያ ኢባርዛባል (2፡04.17) በሁለት ሰከንዶች ተቀድማ 2፡04.19 በሆነ ጊዜ በሁለተኛነት ውድድሯን አጠናቅቃለች፡፡

ስዊዘርላንዳዊቷ ጆሴሊን ዊንድ 4፡08.87 በሆነ ሰዓት የቦታውን ሪከርድ ሰብራ ባሸነፈችበት የ1500 ሜትር ሴቶች፤ ኢትዮጵያዊያቱ ፅጌ ተሾመ (4፡10.65)፣ ቅስነት አለም (4፡11.96) እና አክሱማዊት እምባዬ (4፡14.28) ከ4ኛ-6ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቅቀዋል፡፡

በ3000 ሜትር ወንዶች አጭር ትራክ ደ/አፍሪካዊው ሴፖ ሲቴ 7፡50.87 በሆነ ጊዜ የቦታውን ሪከርድ ሰብሮ ሲያሸንፍ፤ ኢትዮጵያዊው ኃይለማሪያም አማረ ደግሞ በ7፡55.06 ኬንያዊውን ኢስማኤል ኪፕኪሩይን (7፡51.05) በመከተል 3ኛ ወጥቷል፡፡

ምስጋናው ታደሰ

የካቲት 05/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *