የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት አስር አዳዲስ የጸጥታ ምክር ቤት አባላትን መረጠ By Ethio AdminFebruary 12, 2026February 12, 2026የሀገር ውስጥ ዜና ምክር ቤቱ ሶማሊያ እና ኡጋንዳን ከምስራቅ አፍሪካ፣ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ጋቦንን ከማዕከላዊ አፍሪካ፤ ቤኒን፣ ኮትዲቯር እና ሴራሊዮንን ከምዕራብ አፍሪካ፣ ሞሮኮን ከሰሜን፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሌሴቶን ደግሞ ከደቡባዊ አፍሪካ አባል አድርጎ መርጧል። ሀገራቱ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ምክር ቤቱን በአባልነት ያገለግላሉ። የካቲት 05/2018 ዓ.ም