“ያልታሰበው ሲሳይ”

የአቢሲኒያ ባንክ “ያልታሰበው ሲሳይ” በሚል መሪ ቃል ላለፉት አምስት ወራት ሲያካሂድ የቆየው የሽልማት መርሃ-ግብር ለባለዕድለኛው የአፓርትመንት ቁልፍ በማስረከብ ተጠናቀቀ።

ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በወጣው ዕጣ፣ አቶ መሐመድ ከድር የባለ ሁለት መኝታ አፓርትመንት ዕድለኛ መሆናቸው የሚታወስ ሲሆን ባለዕድለኛው ዛሬ አዲስ አበባ አያት አካባቢ የሚገኘውን የመኖሪያ ቤቱን ቁልፍ ከባንኩ የሥራ ኃላፊዎች ተረክበዋል።

አቶ መሐመድ ሽልማቱን በተቀበሉበት ወቅት በሰጡት አስተያየት፤ ቤቱ ትልቁን የሕይወት ሕልማቸውን ያሳካላቸው መሆኑን ገልጸው፣ ለአቢሲኒያ ባንክ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የባንኩ የዲጂታል ግብይት ቺፍ ወይዘሪት ሶስና መንገሻ በበኩላቸው፤ የመርሃ-ግብሩ ዋና ዓላማ ደንበኞች የዲጂታል ግብይት ሥነ-ምህዳር ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማበረታታት መሆኑን ገልጸዋል።

ዲጂታል ፋይናንስ በባንክ እና በደንበኞች መካከል ያለውን የርቀት እና የጊዜ ክፍተት የሚደፍን ድልድይ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።

በመጨረሻም፣ በኢትዮጵያ የዲጂታል ገንዘብ ግብይት እያደገ መምጣቱን የጠቀሰው የብሔራዊ ባንክ መረጃ፤ ዓመታዊ የዝውውር መጠኑ 12 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር መድረሱን አመልክቷል።

አቤል እስጤፋኖስ

የካቲት 05/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *