በአዳማ ሪጅን አርሲ ዞን ጄጁ ወረደ ዶኒ ቀበሌ ውስጥ በሚገኘው” ተስፈ ህይወት” አካባቢ ለመስኖ አገልግሎት የሚውል 200 ኪ.ቮ.አ/15 ኪ.ቮ.አ ትራንስፎርመር ባልታወቁ ግለሰቦች መሰረቁ ተገለፀ።
የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ጣሃ አህመድ እንደገለፁት ክስተቱ የተከሰተው የካቲት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 5 ሰዓት አካባቢ መሆኑን ተናግረዋል።
በጉዳቱ ምክንያት ለመስኖ አገልግሎት ይቀርብ የነበረ የኃይል አቅርቦት መቋረጡን ነዉ ዳይሬክተሩ የገለፁት።
በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ላይ በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለው የስርቆት ድርጊት የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንቅፋት እየፈጠረ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ እየተገለፀ ይገኛል።
የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን መስረቅ በሕግ የሚያስቀጣ በመሆኑ ሕብረተሰቡ እንዲህ አይነት ድርጊት ሲፈጸም ሲመለከት ለሕግ አስከባሪ አካላት ማሳወቅ እንዳለበት ጥሪ ቀርቧል
የመሰረተ-ልማትና የኃይል ስርቆትን ለመከላከል የሚያግዙ ህጎች መኖራቸውን ቢጠቀስም የህግ ክፍተት ሳይሆን በማስፈፀም በኩል ያሉ ክፍተቶች መኖራቸውን በተደጋጋሚ ይገለፃል፡፡
የካቲት 06/2018 ዓ.ም
