የዩክሬን የቀድሞ የኢነርጂ ሚኒስትር አገሪቱን ለቅቀው ለመውጣት ሲሞክሩ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ባለሥልጣናት ተናገሩ።
ባለፈው ዓመት በሙስና ቅሌት ስማቸው ከተጠቀሱት ባለሥልጣናት መካከል አንዱ የሆኑት እና በኋላ ላይ ከኃላፊነታቸው የተነሱት ጀርመን ጋሉሽቼንኮ፣ ዩክሬንን ለቅቀው ሲወጡ ባቡር ላይ መያዛቸው ተገልጿል።
በኅዳር ወር 100 ሚሊዮን ዶላር የዝርፊያ ወንጀል ውስጥ ከተሳተፉት በርካታ የመንግሥት ሰዎች አንዱ መሆናቸው ተጠቅሷል።
ይህ የሙስና ቅሌት የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪን አስተዳደር ይጥላል ተብሎ ተሰግቶ ነበር።
የዜሌንስኪ አስተዳደር ወደ ሥልጣን የመጣው ሩሲያ ወረራ ከመፈጸሟ በፊት ሙስናን ከአገሪቱ ጠራርጎ ለማጥፋት ቃል በመግባት ነበር።
ለዜሌንስኪ በጦርነቱ ወቅት የቅርብ አማካሪያቸው የነበሩት እና የጽህፈት ቤት ኃላፊው አንድሪ ይርማክ ቤታቸው ከተፈተሸ በኋላ ሥልጣናቸውን ለቅቀዋል።
ፕሬዝዳንቱም ሆነ ይርማክ ጥፋት ሰርተዋል በሚል አልተከሰሱም።
ይሁን እንጂ ይህ የሙስና ቅሌት ከተሰማ በኋላ በዩክሬን ሕገ መንግሥት መሠረት እአአ ከ2022 ጀምሮ በሩሲያ ወረራ ምክንያት ሳይካሄድ የቀረውን ምርጫ እንድታካሂድ ከአሜሪካ የሚደርሰውን ጫና በርትቷል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።
የካቲት 09/2018 ዓ.ም
