ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርሱ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተቀብለዋቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሰራጩት የእንኳን ደህና መጡ ፅሁፍ ” እንኳን ወደ ምድረ ቀደምቷ ሀገር ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ ” ብለዋቸዋል።
” ይህ ይፋዊ የስራ የጉብኝት ልውውጣችን በቱርክዬ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ጥልቅ የአጋርነት ጥንካሬ የሚያንጸባርቅ ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።
” ከአንካራ እስከ አዲስ አበባ፤ በሁለቱ ጥንታዊ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክሩ እና ዘላቂ ትስስርን የሚያረጋግጡ ውጤታማ ውይይቶች እንዲኖሩን እመኛለሁ ” ብለዋል።
የካቲት 10/2018 ዓ.ም
