ከአሸባሪ ቡድኖች እና ከሌሎች የታጠቁ ቡድኖች ጋር በሚደረገው ውጊያ ወታደሮችን ለማሰልጠን እንዲያግዙ ወደ 1መቶ የሚጠጉ የአሜሪካ ወታደሮች ናይጄሪያ ደርሰዋል።
የናይጄሪያ ጦር ኃይል አሜሪካንን ለሥልጠና፣ ለቴክኒክ ድጋፍ እና ለመረጃ ልውውጥ እንድታግዘው መጠየቁን ገልጿል።
የአሜሪካ ወታደሮች በውጊያ ውስጥ እንደማይሳተፉ ወይም ቀጥተኛ የኦፕሬሽን ሚና እንደማይኖራቸው የገለጸው ጦር ኃይሉ፤ የናይጄሪያ ኃይሎች ሙሉ የዕዝ ሥልጣን እንደሚኖራቸው አስታውቋል።
የናይጄሪያ መንግሥት በአገሪቱ ሰሜን ምዕራብ ከሚንቀሳቀሱ በደርዘን የሚቆጠሩ የታጠቁ ቡድኖች ጋር የረጅም ጊዜ ውጊያ እያካሄደ ይገኛል።
በታኅሣሥ ወር የአሜሪካ ኃይሎች በክልሉ ከአይ ኤስ ጋር ግንኙነት ባላቸው ታጣቂዎች ላይ የአየር ጥቃት ሰንዝረው ነበር።
እስከዳር ግርማ
የካቲት 10/2018 ዓ.ም
