ኦክሽን ኢትዮጵያ አዲስ የዲጂታል ጨረታ ወኪሎች (DAA) ፕሮግራም ይፋ ሊያደርግ ነው

ኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማኅበር በኢትዮጵያ የዲጂታል ግብይትን ይበልጥ ለማሳለጥ ያለመ “Digital Auction Agent” (DAA) የተሰኘ አዲስ ፕሮግራም በይፋ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።

የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ዮሴፍ አንኩ  ባለፉት ሁለት የሥራ ዓመታት ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት የተፈጸመበትንና ከ100 ሺህ በላይ ተጠቃሚዎችን ያሳተፈ የዲጂታል ጨረታ ፕላትፎርም ሲያስተዳድር ቆይቷል።

አሁን ደግሞ ይህንን የቴክኖሎጂ ስኬት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ፣ በግብርና ምርቶችና በከብት ሀብት (Livestock) ግብይት ላይ የሚያተኩሩ የዲጂታል ወኪሎችን ለማሰማራት ዝግጅቱን አጠናቋል።

እንደ ድርጅቱ ገለጻ፣ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ 100 ሺህ የሚሆኑ የዲጂታል ጨረታ ወኪሎችን በመላ ሀገሪቱ ለማሰማራት ታቅዷል።

ይህም “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” እና ሀገራዊ የኢ-ኮሜርስ ስትራቴጂን ዳር ለማድረስ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።

ኦክሽን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከጉምሩክ ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ከኢትዮ ቴሌኮም እና ከሌሎች መንግሥታዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።

ልኡል ወልዴ

የካቲት 13/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *