ትናንት በእንግሊዝ በተካሄደው የሴቶች የኤፍ.ኤ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ የቼልሲ እንስቶች የማን.ዩናይትድ አቻቸውን 2-1 አሸንፈዋል።

ሁለቱ ቡድኖች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1-1 ነበር ያጠናቀቁት።

የሰማያዊዎቹ የአሸናፊነት ጎል የተመዘገበችው በጭማሪ ሰዓት 99ኛው ደቂቃ ላይ ነበር። የጎሏ ባለቤት ደግሞ ትውልደ ኢትዮጵያዊ/አሜሪካዊቷ ናኦሚ ግርማ ናት።

ናኦሚ ይህ የመጀመሪያ የቼልሲ ጎሏ ሆኖ የተመዘገበላት ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪም የጨዋታው ኮከብ ተብላ ተሸልማለች።

ምስጋናው ታደሰ

የካቲት 16/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *