የኢራን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት እራሳቸው ‹‹የውሸት ዜና ሰለባ ሆነዋል›› ብለዋል።
ቴህራን ወደ አሜሪካ ዋና መሬት ሊደርስ የሚችል ሚሳኤል እየሠራች ነው በማለት የቀረበዉን ክስ አስተባብለዋል፡፡
የኢራን ሚሳኤሎች ‹‹በተፈጥሮ ተከላካይ››ናቸው ሲሉም ተናግረዋል።
ኢራን ወደ አሜሪካ የሚደርሱ ሚሳኤሎችን እየሰራች አይደለም ያሉት አራግቺ፤ ሚሳኤሎቻችን በተፈጥሯቸው ተከላካይ ናቸው እነሱ የተገነቡት ራሳችንን እንድንከላከል ነዉ ብለዋል፡፡
በእነርሱ እይታ ድርጊቱ ህገወጥ ነው ተብሎ ሊወሰድ ይችላል ያሉት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ነገርግን በእኛ እይታ ራስን የመከላከል ማዕቀፍ ውስጥ ያለ ህጋዊ ድርጊት ነበር ማለታቸዉን አልጀዚራ ዘግቧል።
ሊዲያ ደሳለኝ
የካቲት 19/2018 ዓ.ም
