አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በሰብአዊ መብት ላይ ችግሮች እየፈጠረ እንዳለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ

ኮሚሽኑ በተለይም ከጥላቻ ንግግር እና መሠል ድርጊቶች ጋር በተያያዘ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሰብዓዊ መብቶች ላይ ችግሮች ሊፈጥር ስለመቻሉ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ እንደገለፁት፤ ዘመናዊ የሆኑ የህግ ማዕቀፎች ቢኖሩንም የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እየሄደበት ያለዉ ፍጥነት ከነዚህ ማዕቀፎች ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም ብለዋል፡፡

ዋና ኮሚሽነሩ ሲቀጥሉም በእነዚህ ዙሪያ የስትራቴጂክ ፕላኑን ጭምር እንደገና መከለስ የሚያስፈልገዉ እንደሆነ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ፤”እንደ አጋጣሚ ሆኖ በዚህ አመት ሰኔ ወር ላይ ነዉ የአምስት አመቱ ስትራቴጂክ ፕላናችን የሚያበቃዉ፤ ይህንን ተከትሎ በአዲሱ ስትራቴጂክ ፕላናችን ላይ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አቅጣጫዎች እንናስቀምጣለን ብለን እየሄድንበት ነዉ ያለዉ”ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በሰብዓዊ መብት ዙሪያ ፈታኝ እየሆኑ መጥተዋል የተባሉት ንግድ እና ሰብአዊ መብት፣አካባቢ ጥበቃ እና ሰብዓዊ መብት ዙሪያ ያሉ ችግሮች በአዲሱ ስትራቴጂካዊ ፕላን አቅጣጫ የሚሰጥባቸዉ ይሆናሉ ተብሏል።

ቁምነገር አየለ

የካቲት 19/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *