በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር መካከል ያለው ግንኙነት መሻከሩም ተዘግቧል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የብሪታንያውን ጠቅላይ ሚኒስትር “ተሸናፊ” ሲሉ መጥራታቸውን ቴሌግራፍ የዘገበ ሲሆን፤ በተጨማሪም ስታርመር “እንደ ዊንስተን ቸርችል አይደሉም” በማለት በይፋ ተችተዋቸዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት እየጎዱት ነው ሲሉ ከሰዋል።
ለአለመግባባቱ መነሻ የሆነው ብሪታንያ የአሜሪካ ጦር በኢራን ላይ ለሚሰነዝረው ጥቃት የእንግሊዝን የጦር ሰፈሮች ለመጠቀም ያቀረበችውን ጥያቄ መጀመሪያ ላይ ውድቅ ማድረጓ እንደሆነ ተገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር ለትችቱ በሰጡት ምላሽ፤ በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች ከብሪታንያ የጦር ሰፈሮች እየተነሱ ኦፕሬሽን እያከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
የብሪታንያ ጄቶችም የአሜሪካን ኃይሎች በመከላከል ረገድ እገዛ እያደረጉ መሆኑን የጠቀሱት ስታርመር፤ ይህ ሁኔታ “ልዩ ግንኙነታችን በተግባር እየታየ መሆኑን ማሳያ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ የሁለቱ መሪዎች ግጭት በዓለም አቀፍ ፖለቲካ እና በደህንነት ትብብር ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ በብዙዎች ዘንድ ስጋትን እየፈጠረ ይገኛል።
ልዑል ወልዴ
የካቲት 27/2018 ዓ.ም
