የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ፤ የሀገሪቱ አንጋፋ ባንክ የሆነው “ባንክ ሴፓህ”የዳታ ማዕከል ላይ የቦምብ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቀዋል።
ጥቃቱ የተፈጸመው ሰራተኞች ለኢራን አዲስ ዓመት በዓል የደመወዝ ክፍያ በማዘጋጀት ላይ ባሉበትና ቢሮው በሰው ተሞልቶ በነበረበት ወቅት መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
አባስ አራግቺ ይህንን ድርጊት “ከባድ ወንጀል” ሲሉ የገለጹት ሲሆን፥ የኢራን ጦር ለዚህ ጥቃት ተመጣጣኝ የሆነ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስድና በጥቃቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት ዋጋቸውን እንደሚያገኙ አስጠንቅቀዋል።
ጥቃቱ የተሰነዘረው በቴህራን በሚገኘው የባንኩ ቅርንጫፍ ላይ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፥በወቅቱ የነበረውን የጉዳት መጠን በተመለከተ ግን ዝርዝር መረጃ አልተሰጠም።
ልዑል ወልዴ
መጋቢት 03/2018 ዓ.ም
