የደቡብ ሱዳን ጦር በተቃዋሚዎች እጅ የነበረችውን ትልቅ ከተማ መልሶ መቆጣጠሩን አስታወቀ

የደቡብ ሱዳን መንግሥት ጦር ኃይሎች በተቃዋሚዎች እጅ የነበረችውን የአኮቦ ከተማን መልሰው መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ይህች ከተማ አገሪቱን ወደ ሙሉ የእርስ በርስ ጦርነት አፋፍ ባደረሰው በተቀናቃኝ ጦሮች መካከል ለሚካሄደው ውጊያ የቅርብ ጊዜ የግጭት መድረክ ሆና ቆይታለች።

‹‹አኮቦ ሰላም ናት፣ አካባቢዋም ሰላም ነው›› ሲሉ የደቡብ ሱዳን ሕዝብ መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ ጄኔራል ሉል ሩአይ ኳንግ በዋና ከተማዋ ጁባ ገልጸዋል።

ጦሩ ጥቃቱን ከመሰንዘሩ በፊት ለሰላማዊ ሰዎች፣ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቋማት እና ለእርዳታ ሠራተኞች አካባቢውን እንዲለቁ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር።

በዚህም ምክንያት ወደ 200 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ወደ ጎረቤት አገር ኢትዮጵያ ተሰደዋል።

ደቡብ ሱዳን በ2011 ነፃነቷን ብታገኝም፣ ብዙም ሳይቆይ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የገባች ሲሆን፤ አሁንም በከፍተኛ ድህነት እና በሙስና እንደተዘፈቀች ትገኛለች።

በፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና በረጅም ጊዜ ተቀናቃኛቸው ሪክ ማቻር መካከል በ2018 የተፈረመው የሥልጣን ክፍፍል ስምምነት ከ2025 መጀመሪያ ጀምሮ እየፈረሰ ሲሆን፤በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶች በመከሰታቸው ወደ ሙሉ ጦርነት ሊመለሱ ይችላሉ የሚሉ ስጋቶች እየጨመሩ መጥተዋል።

ሀና ሰይፉ

መጋቢት 03/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *