የአሜሪካው የኢነርጂ ሚኒስትር በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ለተሰራጨ የተሳሳተ መረጃ ሃላፊነት ወሰዱ

የአሜሪካው የኢነርጂ ሚኒስትር ክሪስ ራይት፣ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ በወጣ የተሳሳተ መረጃ ምክንያት ሃላፊነት እንደሚወስዱ አስታወቁ።

በሚኒስትሩ ይፋዊ የኤክስ (የቀድሞው ትዊተር) ገጽ ላይ ሰሞኑን በወጣ ጽሁፍ፤ የአሜሪካ የባህር ኃይል በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በኩል የነዳጅ ጫኝ መርከብን በታጀበ ሁኔታ ማሳለፉን የሚገልጽ መረጃ ሰፍሮ ነበር።

ይሁን እንጂ መረጃው ስህተት መሆኑና እንዲህ ያለ የጥበቃ ስራ አለመከናወኑ ከተረጋገጠ በኋላ ሚኒስትሩ ለተፈጠረው ስህተት ሙሉ ሃላፊነቱን ወስደዋል።

ክሪስ ራይት መረጃው በስህተት እንዲወጣ ያደረገው በጽህፈት ቤታቸው ውስጥ የተፈጠረ የኮሙኒኬሽን ክፍተት መሆኑን ገልጸው፤ ለወደፊቱ መሰል ስህተቶች እንዳይደገሙ ጥንቃቄ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ለዓለም አቀፍ የነዳጅ ንግድ እንቅስቃሴ እጅግ ስትራቴጂካዊ እና ስሱ ስፍራ በመሆኑ፣ በቦታው ላይ የሚደረጉ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን የሚመለከቱ መረጃዎች በከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚታዩ ይታወቃል።

የኢነርጂ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት መረጃው መሳሳቱን አምኖ ከገጹ ላይ ያነሳው ቢሆንም፣ በወቅቱ መረጃው በበርካታ ወገኖች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

ልዑል ወልዴ

መጋቢት 04/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *