የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ጥላሁን እንደገለጹት፤ ሰዓት በማያከብሩ ሰራተኞች ላይ አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድና የሲቪል ሰርቪስ ስርዓቱ እየጠነከረ በመምጣቱ ሁሉም ሰራተኛ በስራ ቦታው ተገኝቶ ስራውን በአግባቡ ማከናወን እንዳለበት አሳስበዋል።
ተቋሙ እንደፈለጉ የሚገቡበትና የሚወጡበት ስፍራ ሳይሆን በስርዓት መመራት ያለበት መሆኑን በመጠቆም የጣት አሻራ መቆጣጠሪያው በማዕከልና በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በቅርቡ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።
ለጣት አሻራ ስርዓቱ መከበርም ከሰው ሀይል ዳይሬክቶሬት በተጨማሪ የየዘርፉ ዳይሬክቶሬቶችና ቡድን መሪዎች የቅርብ ክትትል እንዲያደርጉ ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።
የሰው ሀይል ዳይሬክቶሬት ተወካይ ዳይሬክተር አቶ በቀለ ጉድሳ በበኩላቸው የዲጂታል መቆጣጠሪያው ዋና አስፈላጊነት የሰራተኞችን የመግቢያና መውጫ ሰዓት ለመቆጣጠርና የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማሳለጥ መሆኑን ገልጸው በዚህም መሠረት ሰራተኞች በቀን አራት ጊዜ ማለትም ጠዋት በ2:45፣ ለምሳ መውጫ ከ6:30 እስከ 7:00፣ ከምሳ መልስ ከ7:01 እስከ 7:45 እንዲሁም በስራ መውጫ ሰዓት 11:45 ላይ የጣት አሻራቸውን ማሳረፍ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል።
ይህ የአፈጻጸም ማኑዋል በተለያዩ ምክንያቶች ፈቃድ ላይ ያሉ፣ የመስክ ስራ የሚሰሩ፣ ልዩ የስራ ባህሪ ያላቸውን ሰራተኞችና ድንገተኛ አደጋዎችን ከግንዛቤ ያስገባ መሆኑንም አቶ በቀለ አብራርተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አመራሮችና ሰራተኞች በዲጂታል የጣት አሻራ የስራ ሰዓት መቆጣጠሪያ የአፈጻጸም ማኑዋል ላይ ሰፊ ውይይት አካሂደዋል።
መጋቢት 07/2018 ዓ.ም
