ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ እንደተነጋሩ  አስታወቁ ።

“ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነትና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ የስልክ ውይይት አድርገናል”  ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ።

የሩሲያ ፕሬዚዳንት የፕሬስ ፀሐፊ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ሁለቱ መሪዎች መነጋገራቸውን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ፑቲን በኢትዮጵያ ውስጥ የደረሰውን የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋ አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት እና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀዘን መግለጫ (https://t.me/sputnik_ethiopia/22190) እንደላኩም አስታውቀዋል።

መጋቢት 07/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *