የአሜሪካ ጦር በኢራን የተመሸጉ የሚሳኤል ጣቢያዎች ላይ ጥቃት ሰነዘረ

የአሜሪካ መካከለኛ ዕዝ ባወጣው መግለጫ፤በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ አቅራቢያ በሚገኙ የኢራን የባህር ጠረፎች ላይ ያነጣጠረ መጠነ ሰፊ የአየር ድብደባ መፈጸሙን አስታዉቋል።

በዚህ ጥቃት አሜሪካ እያንዳንዳቸው 5 ሺህ ፓውንድ የሚመዝኑና መሬት ውስጥ ዘልቀው የሚገቡ ቦምቦችን የተጠቀመች ሲሆን፤ኢላማ የተደረጉትም በጠንካራ ሁኔታ የተመሸጉ የኢራን ሚሳኤል ጣቢያዎች መሆናቸው ተገልጿል።

እንደ መካከለኛ ዕዝ መግለጫ ከሆነ፤ጥቃቱ የተፈጸመው በዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦች እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ስጋት የደቀኑትን የኢራን የባህር ላይ ተመዝጋቢ ሚሳኤሎችን ለማውደም ነው።

የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ለዓለም አቀፍ የነዳጅና የንግድ ልውውጥ ወሳኝ ስፍራ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤አሜሪካ ይህንን ጥቃት የፈጸመችው የባህር ላይ ትራንስፖርት ደህንነትን ለማረጋገጥ መሆኑን ገልጻለች።

እስከ አሁን ከኢራን በኩል የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ የለም።

ልዑል ወልዴ

መጋቢት 09/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *