ታላላቅ የሀገራችንን አትሌቶች ለዓለም አትሌቲክስ ያበረከተው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ መጋቢት 15/2018 ዓ.ም በአደይ አበባ ስቴዲየም ይጀመራል። By Ethio AdminMarch 23, 2026March 23, 2026የሀገር ውስጥ ዜና ዘንድሮ ለ55ኛ ጊዜ በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ 621 ወንዶችና 436 ሴቶች በድምሩ 1057 አትሌቶች ተሳታፊ ይሆናሉ። ለውድድሩ በአጠቃላይ 10 ሚሊዮን ብር በጀት የተመደበለት ሲሆን ከዚህ ውስጥም 580,000 ብሩ ለአሸናፊ አትሌቶች በሽልማት መልክ የሚበረከት ይሆናል። ሻምፒዮናው እስከ መጋቢት 20/2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ይሆናል። ምስጋናው ታደሰ መጋቢት 14/2018 ዓ.ም