ግብፅ የኢራንን ጦርነት ለማርገብ የሚደረጉ ስብሰባዎችን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገለጹ

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ሀገራቸው በኢራን እና በአሜሪካ መካከል የምታደርገው ሽምግልና ከፓኪስታን እና ቱርክ ጋር በመተባበር ቀጥሏል ብለዋል።

አክለውም ጦርነቱ ማብቃት ያለበት አንዱ አሸንፎ ሌላው በሚሸነፍበት ሳይሆን ሁለቱም ወገኖች ተጠቃሚ በሚሆኑበት ሁኔታ ላይ ተመስርቶ መሆን አለበት ሲሉ ገልጸዋል።

በተጨማሪም በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለውን ጦርነት ለማርገብ የሚደረጉ ማናቸውንም ስብሰባዎች ለማስተናገድ ግብፅ ፈቃደኛ መሆኗን ገልጸዋል።

በካይሮ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ አብደላቲ የድርድር ዕድሎች እያለቁ ሊሆን እንደሚችል በማስጠንቀቅ፤በአሜሪካ እና በኢራን ተወካዮች መካከል ቀጥተኛ ስብሰባ እንዲደረግ አሳስበዋል።

ይህን ጦርነት አንዱ አሸንፎ ሌላው በሚሸነፍበት ሳይሆን ሁለቱም ወገኖች በሚጠቀሙበት ሁኔታ ማቆም እንችላለን ብለዋል አብደላቲ።

ኢራን በዶናልድ ትራምፕ መንግስት ረቡዕ ዕለት የቀረበላትን የመጀመሪያውን የተኩስ አቁም የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ አድርጋለች።

ይሁን እንጂ የኢራን ባለስልጣናት በሚቀጥለው ሳምንት በፓኪስታን ኢስላማባድ ሊካሄድ የሚችለውን ከአሜሪካ ተደራዳሪዎች ጋር የሚደረግ ስብሰባ እያሰቡበት እንደሆነ የሚገልጹ ዘገባዎች አሉ።

ግብፅ አሜሪካ ለድርድር ያቀረበችውን ተነሳሽነት እንደምትደግፍም አሳይታለች።

እስከዳር ግርማ

መጋቢት 17/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *