የ-AI ተዋናዮች በቻይና የፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ ያስነሱት አዲስ ውዝግብ

በቻይና የሚገኘው ዩሁግ ሚዲያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የሚሰሩ ተዋናዮችን ይፋ ማድረጉ በፊልም ኢንዱስትሪው ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብ ቀስቅሷል።

ቺን ሊንዩ እና ሊን ዢያን የተባሉት እነዚህ ዲጂታል ተዋናዮች ከእውነተኛ የቻይና የፊልም ኮከቦች ጋር አስገራሚ መመሳሰል ያላቸው ሲሆን፣ በማህበራዊ ሚዲያም ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ከአድናቂዎቻቸው ጋር መገናኘት ጀምረዋል።

ይሁን እንጂ ይህ ቴክኖሎጂ እንደ ሜካፕ ባለሙያዎች፣ ረዳት ተዋናዮችና ሌሎች የፊልም ሰራተኞችን ከስራ ያፈናቅላል የሚል ከፍተኛ ስጋት በብዙዎች ዘንድ አሳድሯል።

ምንም እንኳን አንዳንድ የዘርፉ ባለሙያዎች ወጪን ለመቀነስና አደገኛ ትዕይንቶችን ለመተካት የ-AI ተዋናዮችን መጠቀምን ቢደግፉም፣ ተቺዎች ግን የኪነ ጥበብ ስራ የሰውን ልጅ ስሜትና ነፍስ ይፈልጋል ይላሉ።

ይህ በቻይና የታየው አዲስ ነገር በምዕራቡ ዓለምም እየተለመደ የመጣ ሲሆን፣ የሰው ልጅ የፈጠራ ችሎታ ከቴክኖሎጂው ጋር እንዴት ተደጋግፎ ሊቀጥል ይችላል የሚለው ጥያቄ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡

ሐመረ ፍሬው

መጋቢት 21/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *