የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት ይረግባል የሚል ተስፋ በመኖሩ እና የዶላር ዋጋ በመቀነሱ ምክንያት የወርቅ ዋጋ መጠነኛ ጭማሪ እያሳየ መሆኑ ተገልጿል።
በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ያለው ጦርነት በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሊያበቃ ይችላል የሚል መግለጫ መውጣቱን ተከትሎ የዶላር ዋጋ በመዳከሙ ሚያዝያ 1 ቀን 2026 የወርቅ ዋጋ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።
አሁን ላይ የወርቅ ስፖት ዋጋ በ1በመቶ ጭማሪ በማሳየት 4ሺ 7 መቶ 17.82 ዶላር ደርሷል፤ ይህም ከመጋቢት 20 ጀምሮ የታየ ከፍተኛው የዋጋ መጠን ነው።
ለሚያዝያ ወር የሚቀርበው የወርቅ ግብይት ደግሞ በ1.4 በመቶ ጭማሪ በማሳየት 4ሺ7መቶ 44.30 ዶላር ደርሷል።
ይህ የዋጋ ጭማሪ የታየው በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ሊረግብ ይችላል የሚል ተስፋ በመኖሩ ባለሀብቶች ወደ ወርቅ ግብይት ፊታቸውን በማዞራቸው ነው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል::
ሳራ ዮሐንስ
መጋቢት 23/2018 ዓ.ም
