በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለዉ የትግራይ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ እና የተሳታፊዎች ልየታ ሂደትን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዛሬዉ ዕለት አስጀምሯል።
ከተሳታፊዎች ጋር ዉይይት እያደረገ ያለዉ ኮሚሽኑ ከተወካዮች ጥያቄዎች ቀርበዉለታል።
ለኮሚሽኑ ጥያቄ ካቀረቡት መካከል ከትግራይ ዲሞክራሲ ፓርቲ የመጡት አቶ ሙሉ ብርሃን የትግራይ ህዝብ በእገታ ዉስጥ እንዳለ የሚታወቅ ነዉ ብለዋል።
ይህንን የኮሚሽኑን ጥሪ በተመለከተም “በትግራይ እንዳንመካከር፥ ወደ አዲስ አበባም ሄደን እንዳንወያይ መግለጫም ወጥቷል “ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ሙሉ ብርሃን አክለዉም ይህ የምክክር ኮምሽኑ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ካለዉ ሂደት በፊት በዋነኝነት ኮሚሽኑ እንዴት ወደ ትግራይ መግባት አለበት? የሚለዉን ማወቅ ያስፈልገናል ሲሉ ሀሳባቸዉን ሰጥተዋል።
ከክልሉ ተወክለዉ የመጡ እንዲሁም የትግራይ ተወላጆች የትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታን ጨምሮ በሚቀጥሉት ቀናት ስለሚኖረዉ ሂደት እንዲሁም ሌሎች ጉዳዩችን ዙሪያ ለኮሚሽነሮች ጥያቄን እያቀረቡ ዉይይት እየተደረገ ይገኛል።
ቁምነገር አየለ
መጋቢት 23/2018 ዓ.ም
