የአሜሪካ መካከለኛው ዕዝ (CENTCOM) ባወጣው የቅርብ ጊዜ መግለጫ፣ በኢራን ላይ እየተካሄደ ያለውን ወታደራዊ ዘመቻ ተከትሎ የቁጥራዊ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል።
እንደ መግለጫው ከሆነ፣ “ኦፕሬሽን ኤፒክ ፊዩሪ” (Operation Epic Fury) ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ በአጠቃላይ ከ12 ሺህ በላይ የአየር ላይ የውጊያ በረራዎች ወይም ተልዕኮዎች ተከናውነዋል።
ይህ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአየር ላይ እንቅስቃሴ፣ አሜሪካ በኢራን ላይ እያደረገች ያለውን ወታደራዊ ጫና ስፋት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።
እነዚህን ከ12 ሺህ በላይ በረራዎች ያከናወኑት የባህር ኃይል ተዋጊ ጄቶች፣ አሁንም ለተጨማሪ አዳዲስ የውጊያ በረራዎች እና ጥቃቶች ዝግጁነታቸውን እያጠናቀቁ መሆኑን የአሜሪካ መካከለኛው ዕዝ አረጋግጧል።
ይህ በኢራን ላይ ያነጣጠረውና በሺዎች የሚቆጠሩ በረራዎች የተከናወኑበት ኦፕሬሽን፣ ቀጣይነቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ከሴንትራል ኮማንድ የተሰጠ ዝርዝር መረጃ የለም።
ልዑል ወልዴ
መጋቢት 23/2018 ዓ.ም
