አሜሪካ እና ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት በማድረጋቸው የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ቀነሰ

የዓለም አቀፍ የአክሲዮን ገበያም መነቃቃት አሳይቷል

አሜሪካ እና ኢራን ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን እና ቴህራን ወሳኝ የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥ ለጊዜው ለመክፈት መስማማቷን ተከትሎ፤ረቡዕ ዕለት የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል፤ አክሲዮኖች ደግሞ ጭማሪ አሳይተዋል።

ኢራን የውሃ መስመሩን እንድትከፍት ዶናልድ ትራምፕ ያስቀመጡት የጊዜ ገደብ ሊያበቃ ሲቃረብ ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ የጥቃት ማቆም ውሳኔ ማድረጋቸውን እና ‹‹ሊተገበር የሚችል››ባለ 10 ነጥብ የውሳኔ ሃሳብ መቀበላቸውን አስታውቀዋል።

ኢራንም የአለም አንድ አምስተኛው የነዳጅ እና የጋዝ ምርት የሚያልፍበት በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል አስተማማኝ የመተላለፊያ መንገድ ለመስጠት መስማማቷን ገልጻለች።

አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ በከፈቱት ጦርነት ህጻናትን ጨምሮ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ተገድለዋል፡፡

አብዛኛው የኢራን መሰረተ ልማት እና ወታደራዊ ይዞታዎችም ወድመዋል።

ኢራን በበኩሏ እስራኤልን እና የአሜሪካ ጦር ሰፈር የሚገኝባቸውን የክልሉን አገራት በሚሳኤል እና በድሮን በመምታት ምላሽ ሰጥታለች።

ሳራ ዮሐንስ

መጋቢት 30/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *