ማርኮ ሩቢዮም በውይይቱ ላይ ይሳተፋሉ
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት፣ የሊባኖስ አምባሳደር ናዳ ሃማዴህ እና የእስራኤል አምባሳደር የቺኤል ላይተር ቀጥተኛ ድርድር ለመጀመር በዋሽንግተን ዲሲ ይገናኛሉ።
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከሁለቱ አምባሳደሮች ጋር በሚደረገው በዚህ ‹‹የሥራ ደረጃ››ድርድር ላይ እንደሚሳተፉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ውይይቱ እስራኤል ከፍተኛ የአየር ድብደባ እና የምድር ወረራ እያካሄደችባት ባለችው ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲወርድ፣ ሄዝቦላህ ትጥቅ እንዲፈታ እና ሰፋ ያለ የሰላም ዝግጅት እንዲደረግ በሚሉ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል ተብሎ ይጠበቃል።
ሄዝቦላህ የታቀደውን ድርድር ‹‹ከንቱ›› ሲል ውድቅ ያደረገው ሲሆን፤ የሊባኖስ መንግሥት ትኩረቱን የእስራኤልን ‹‹ጥቃት››በመመከት ላይ እንዲያደርግ አሳስቧል።
ሊዲያ ደሳለኝ
መጋቢት 06/2018 ዓ.ም
