ዳሽን ባንክ የ30 ዓመታት ምስረታውን አስመልክቶ ያስናደውን ኤክስፓ በይፋ አስጀመረ

ዳሸን ባንክ በዛሬው እለት በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የተመሰረተበትን 30ኛ አመት ምክንያት ያደረገ ኤክስፓን አስጀምሯል፡፡

ለዘጠኝ ቀናት በሚቆየው በዚህ ኤክስፖ የዳሸን ባንክን የ30 ዓመታት የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቢሽንን ጨምሮ ተጋባዥ የንግድ ተቋማት ምርትና አገልግሎቶቻቸውን የሚያሳዩበት ዐውደ-ርእይ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኗል።

ይህ ዝግጅት ከዕይታም ባለፈ የቢዝነስ ትሥሥር የሚፈጥሩበት፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የሚሞክሩበት እና የነገን የፋይናንስ አቅጣጫ አብረውን የሚቃኙበት መድረክ መሆኑን ባንኩ አስታውቋል፡፡

የባንክ ኢንዱስትሪውን የሚቀይሩ አዳዲስ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ትዕይንቶች፤ በሴት ሥራ ፈጣሪዎች እና በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (SMEs) የሚቀርቡ ምርቶችና አገልግሎቶች፤ለወጣቶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ የፋይናንስ ግንዛቤ ወርክሾፕ፤እንዲሁም ከታላላቅ የዘርፉ ባለሙያዎች እና የኮርፖሬት አጋሮች ጋር ሰፊ የቢዝነስ ትሥሥር (Networking) የሚፈጥሩባቸው ልዩ አጋጣሚዎች በዚህ ኤክስፓ ላለ ይቀርባሉ ተብሏል፡፡

ይህ ዝግጅት እስከ 24 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቀጥል መሆኑን ዳሽን ባንክ አስታውቋል፡፡

የውልሰው ገዝሙ

ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *