በመጪዉ ግንቦት ወር ለሚካሄደው 7ተኛ ሀገራዊ ምርጫ የአንዳንድ የፓለቲካ ፓርቲዎች የተሰጣቸዉን ነፃ የአየር ሰአት በአግባቡ እየተጠቀሙበት እንዳልሆነ ኢትዩ ኤፌም ታዝቧል።
የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ህብረት ለምርጫ የፓርቲዎችን የምርጫ ቅስቀሳ እና የአየር ሰአት አጠቃቀም በተመለከተ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ተናግሯል።
ኢትዩ ኤፌም የህብረት ለምርጫን ዋና ዳይሬክተር አቶ አበራ ሀይለማርያምን የፓለቲካ ፓርቲዎችን ነፃ የአየር ሰአቱን አጠቃቀም በተመለከተ ምን ታዘባችሁ? ሲል ጠይቋል።
አቶ አበራ ” የፓለቲካ ፓርቲዎቹ ነፃ የአየር ሰአቱን በትክክል እየተጠቀሙበት አይደለም ወይ ፥ ስንት ፐርሰቱን ነዉ ያልተጠቀሙበት? እንዲሁም ምክንያታቸዉ ምንድነዉ?” የሚለዉን እያደረጉት ያለዉ ግምገማ የሚያተኩርበት መሆኑን ነግረዉናል።
በተጨማሪም” የገንዘብ ጉዳይ ወይስ የአቅም ማነስ ” የሚለዉን የግምገማ ሪፓርቱ የሚሸፍን መሆኑን ጠቅሰዋል።
ስለዚህ ትክክለኛ ምላሽ እና አስተያየት እንደማይሰጡ ነገር ግን የክትትል ሪፖርቱ ምላሽ እንደሚኖረዉ ተናግረዋል።
ሪፖርቱ የተዛቡ መረጃዎችንና የምርጫ ሽፋን ስርጭቱንም አካቶ እንደሚቀርብ ተገልጿል።
አቶ አበራ እንደገለፁት ሆኖም ፓርቲዎቹ ግን ነፃ የአየር ሰአት ተሰቷቸዋል ፤ ፓርቲዎቹ የሚጠበቅባቸዉ ራሳቸዉን እና ኘሮግራሞቻቸዉን ማስተዋወቅ እንደሆነ ገልፀዋል።
የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ ዋና ዳይሬክተር አቶ አበራ ሃይለማርያም ለኢትዮ ኤፍ .ኤም እንደተናገሩት ፤ ህብረቱ ከ10 በላይ የሚሆኑ የሚዲያ ባለሙያዎችን በማሰማራት የሬዲዮ፣ የቴሌቪዥንና የማህበራዊ ሚዲያ ዘገባዎችን እየገመገመ ይገኛል።
ከ46 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ድምፅ ይሰጡበታል ተብሎ በሚጠበቀው በዚህ ምርጫ፤ 47 የፖለቲካ ፓርቲዎችና ከ70 በላይ የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉ መሆኑ ይታወቃል።
ሂደቱ ፍትሃዊና ሁሉንም አሳታፊ እንዲሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከክልል አመራሮች ጋር ውይይት እያደረገ መሆኑም ተሰምቷል።
ልዑል ወልዴ
ሚያዚያ 19/2018 ዓ.ም
