ጋና በግላዊ መረጃ ጥበቃ ስጋት ምክንያት ከአሜሪካ የእርዳታ ስምምነት ድርድር ራሷን አገለለች

ዋሽንግተን የጋና ዜጎችን የግል መረጃ እንድታገኝ በጠየቀችው መሰረት፤ ጋና ለበርካታ ዓመታት ከሚቆየው የአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ ድርድር መውጣቷን ለፈረንሳይ የዜና አገልግሎት AFP ቅርበት ያለው የሀገሪቱ የመንግስት ምንጭ ገልጿል።እንደ ምንጩ ገለጻ፤ ጋና የአሜሪካን ጥያቄ ውድቅ ካደረገች በኋላ ድርድሩ ተቋርጧል።

ምንጩ አክለውም፤ ጥያቄው ውድቅ ከተደረገ በኋላ የአሜሪካው ተደራዳሪ ቡድን ‹‹ጥላቻ የተሞላበት›› አዝማሚያ ማሳየቱንና ጫና ማብዛቱን ተናግረዋል።

ሮይተርስ እንደዘገበው ከሆነ፤ የታቀደው የእርዳታ ጥቅል ለአምስት ዓመታት የሚቆይና 1መቶ9 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ሲሆን፤በዋናነት ለጤና ዘርፍ የሚውል ሊሆን ይችላል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ስለ ድርድሩ ዝርዝር ሁኔታ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆንም፤ድጋፉ ኤች አይ ቪ/ኤድስን፣ ወባን፣ ሳንባ እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ሊውል ይችል እንደነበር ገልጿል።

የዚህ ድርድር መቋረጥ የመጣው ዋሽንግተን የዩኤስኤአይዲን መዋቅር ካፈረሰች በኋላ፤‹‹አሜሪካ ቀዳሚ የሆነችበት የዓለም አቀፍ ጤና ስትራተጂ›› በሚል አዳዲስ የሁለትዮሽ የጤና ድጋፍ ስምምነቶችን በመላው አፍሪካ እየፈረመች ባለበት ወቅት ነው።

ከዚህ ቀደም ዚምባብዌ እና ዛምቢያ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ውድቅ ያደረጉ ሲሆን፤ የኬንያው ስምምነት ደግሞ በመረጃ ልውውጥ ስጋት ምክንያት በፍርድ ቤት ታግዶ ይገኛል።

ምንም እንኳን በቅርቡ በአክራ እና በዋሽንግተን መካከል ያለው ግንኙነት መሻሻል እያሳየ ቢሆንም ጋና አሁን ድርድሩን አቋርጣለች።

አሜሪካ በበኩሏ አሁንም ከጋና ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልጻለች።

እስከዳር ግርማ

ሚያዚያ 21/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *