ኢንስፔክተሮችን ስራ በሰውነት ላይ በሚታሰሩ ካሜራዎች ለመቆጣጠር የሚያስችል አሰራር ተዘረጋ

በውጭ አገር ስራ ስምሪት ሂደት ውስጥ የሚታየውን የሙስና እና የተገቢነት ጥያቄ ለመመለስ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በየደረጃው ያሉ ተቆጣጣሪዎች ወይም ኢንስፔክተሮች ስራቸውን ሲያከናውኑ በሰውነታቸው ላይ ካሜራ እንዲያስሩ መወሰኑን ገልጿል።

ይህ አሰራር በተለይ በኤጀንሲዎች እና በስልጠና ተቋማት ላይ የሚደረጉ ፍተሻዎች ግልጽ እንዲሆኑ ለማድረግ የታለመ ነው።

ካሜራዎቹ ኢንስፔክተሩ ስራ በጀመረበት ቅጽበት ተገኝቶ እንቅስቃሴውን፣ ንግግሩን እና የሚሰጠውን ውሳኔ በድምፅና በምስል በቀጥታ ወደ ዋናው የቁጥጥር ማዕከል ያስተላልፋል።

ካሜራውን አጥፍቶ ወይም መረጃውን አቋርጦ ስራ መስራት ተጠያቂነትን የሚያስከትል ሲሆን፥ይህም ተቆጣጣሪው ከኤጀንሲዎች ጋር በሚያደርገው ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ያስገድደዋል።

ይህ የቴክኖሎጂ ጣልቃ ገብነት ቀደም ሲል በዘርፉ በቢሊየን የሚቆጠር ብር ይንቀሳቀስበት የነበረውን ህገ-ወጥ የደላላ መረብ ለመበጣጠስ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት በሚኒስቴሩ ከፍተኛ እምነት ተጥሎበታል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *