የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ዙሪያ ጥሪ አቀረቡ

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በኩል ያለውን ችግር በተቀናጀ መልኩ በድጋሚ እንዲከፍቱ ጥሪ አቀረቡ።

ፕሬዝዳንቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሁለቱ ሀገራት በመስመሩ ላይ ያለውን ውጥረት ለማርገብ በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ማክሮን ይህንን ጥሪ ያቀረቡት፤ የአሜሪካ ጦር በመስመሩ በኩል የሚያልፉ የንግድ መርከቦችን የማጀብ ስራ አጠናክሮ በቀጠለበት ወቅት ነው።

የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ለዓለም አቀፍ የነዳጅ እና የንግድ ፍሰት ቁልፍ ስፍራ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ ፕሬዝዳንት ማክሮን መስመሩ በቅንጅት እንዲከፈት መጠየቃቸው በቀጣናው ያለውን ወታደራዊ ፍጥጫ ለመቀነስ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ኢማኑኤል ማክሮን አክለውም፤ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው አለመግባባት በንግድ መርከቦች እንቅስቃሴ ላይ እንቅፋት እንዳይፈጥር ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ሊፈለግለት እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል የዘገበው ሮያ ኒውስ ነው።

ልዑል ወልዴ

ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *