የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሰባት አገራት ጋር የሁለትዮሽ የሥራ ስምሪት ስምምነት መፈረሙን አስታወቀ።
ከካናዳ ጋር የተደረገው ስምምነት የሚጠቀስ እንደሆነ የተነገረ ሲሆንየአዉሮፓ ገበያ ለመቀላቀልም ጥናቶች እየተጠናቀቁ መሆኑ ተገልጿል።
ዜጎች በውጭ አገር የሥራ ገበያ ላይ ከሌሎች አገራት ተቀጣሪዎች ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ፣ የሙያ ስልጠና ጥራትን ማሳደግና የቋንቋ ክህሎትን ማዳበር ላይ ትኩረት ተሰጥቷል ተብሏል።
በተለይም በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚሰጡ ስልጠናዎች በካሜራና በጣት አሻራ የታገዘ ክትትል እንዲደረግባቸው በማድረግ፣ ብቁ የሆኑ ዜጎችን ወደ ውጭ መላክ እንደሚጀመር ተነግሯል።
ዜጎችም ከደላላ ወሬ በመውጣት በሚኒስቴሩ ድረ-ገጽና በ9038 ነፃ የስልክ መስመር በመጠቀም ሕጋዊ መረጃ እንዲያገኙ ጥሪ
ቀርቧል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ግንቦት 03/2018 ዓ.ም
